BBC News, አማርኛ - ዜና
ዜና
የኢትዮጵያ መንግሥትን እንደሚከስሱ ሲናገሩ የነበሩት የቦንድ አበዳሪዎች እንዴት ከስምምነት ደረሱ?
ከአንድ ወር በፊት ለኢትዮጵያ ገንዘብ ያበደሩ ባለሀብቶች የአገሪቱን መንግሥት እንደሚከስሱ አስታውቀው ነበር። ትናንት ሰኞ ሰኔ 22/2018 ዓ.ም. ግን የገንዘብ ሚኒስቴር ከባለሀብቶቹ ጋር የመጀመሪያ ደረጃ ስምምነት መደረሱን አስታውቋል።
ቀጥታ, "ድርድሮች ስኬታማ ከሆኑ በዘላቂነት የተለወጠች ኢራንን ታያላችሁ"- ጄዲ ቫንስ
የአሜሪካ ምክትል ፕሬዝዳንት ጄዲ ቫንስ ከፎክስ ኒውስ ጋር ባደረጉት ቃል ምልልስ “አሜሪካ ከኢራን ጋር በጣም ጥሩ ነጥብ ላይ እንደምትገኝ” ተናገሩ። ከኢራን ጋር የሚደረጉ ድርድሮች ስኬታማ ከሆኑ "የተለወጠች ኢራንን ትመለከታላችሁ" ብለዋል።
የተባበሩት አረብ ኤምሬቶችን ቀጣናዊ ፖሊሲ የለወጠው የኢራን ጦርነት
የተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ከአሜሪካ እና ከእስራኤል ጋር ባላት ግንኙነት የተነሳ የኢራን ዋነኛ ዒላማ ከሆነች በኋላ በቀጣናው አገራት ላይ ያላት መተማመን እየቀነሰች ነው። ለፖለቲካ፣ ለምጣኔ ሃብት እና ሌሎች ፍላጎቷን ለማሟላት ከቀጣናው ውጭ መመልከትን መርጣለች። ለዚህም ከሕንድ፣ ከዩክሬን፣ ከግሪክ፣ ከቆጵሮስ እና ከኢትዮጵያ ጋር ያላትን ትስስር እያጠናከረች ነው።
ቢቢሲ አማርኛ በቲክቶክ
አስተማማኝ ዜና እና መረጃን ቅድሚያ ለማግኘት ቢቢሲ አማርኛን ቲክቶክ ላይ ይከተሉ
የዓለም ዋንጫ - 2026
አዳዲስ ታሪክ የሚመዘገብበት 23ኛው የዓለም ዋንጫ ውድድር ሙሉ መረጃን እዚህ ያገኛሉ
የዓለማችን ትልቁ የእግር ኳስ ውድድር የዓለም ዋንጫ በ23ኛ ዙር ውድድር በርካታ አዳዲስ ነገሮች የሚታዩበት ሆኖ ከሰኔ 4 አስከ ሐምሌ 12 ድረስ ይካሄዳል። በውድድሩ ታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ ሦስት አገራት ውስጥ የሚካሄደውን የዓለም ዋንጫ ተጎራባቾቹ አሜሪካ፣ ሜክሲኮ እና ካናዳ ያስተናግዱታል። የውድድር ቦታዎች፣ ቀናት፣ ሰዓታት፣ ውጤቶች፣ የምድብ ድልድል እና ደረጃ እንዲሁም ሌሎች የጨዋታ ዝርዝር መረሃ ግበሮች እዚህ ይቀርባሉ።
በዓለም ዋንጫ አስሩ ምርጥ የብሔራዊ ቡድኖች ማሊያዎች የትኞቹ ናቸው? ዝነኛ ያደረጋቸው ምንድን ነው?
የዓለም ዋንጫ ምርጥ ማሊያዎች የትኞቹ ናቸው? ምንድን ነው ዝነኛ ያደረጋቸው? ቢቢሲ ስፖርት የምንጊዜም ተወዳጅ 10 ማሊያዎችን በደረጃ አስቀምጧል።
የሐኪም ማስረጃ የሚፈልጉ እና ፊፋ ወደ ዓለም ዋንጫ ስታዲየሞች እንዳይገቡ የከለከላቸው ነገሮች ምንድን ናቸው?
የዓለም ዋንጫ ግጥሚያዎች ወደ ሚካሄድባቸው ስታዲየሞች እንዳይገቡ በርካታ ነገሮች ላይ ክልከላ ጥሏል። እነዚህ የተከለከሉ ነገሮች ምንድን ናቸው? የተለየ ትዕዛዝ እና ፈቃድ የሚያስፈልጋቸውስ የትኞቹ ናቸው?
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቪድዮዎች
የዊግ እና 'ሂውማን ሄር' ከጡት ካንሰር ጋር የሚገናኙ ኬሚካሎች
ፀጉር ላይ የሚቀጠለው ዊግ እና ሂውማን ሄር ከጡት ካንሰር፣ ከሆርሞን መዛባት እንዲሁም በሥነ ተዋልዶ ጤና ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ኬሚካሎችን መያዛቸውን ጥናቶች አሳዩ። ሳይንቲስቶች ዊጎቹ ላይ 50 ጎጂ ኬሚካሎችን አግኝተዋል። እነዚህ ኬሚካሎች ፀጉር ላይ የሚቀጠሉ፣ የሚጠለቁ እንዲሁም የሚሰፉ ዊጎች እና ሂውማን ሄር ላይ ይገኛሉ።
ከጠቅላይ ሚንስትሩ ጋር የሚፎካከሩት ዕጩዎች
በዘንድሮው ሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አሕመድ በኦሮሚያ ክልል ጎማ 2 ምርጫ ክልል ይወዳደራሉ። እርሳቸውን ለማሸነፍ የሌሎች ፓርቲ ዕጩዎችም ይፎካከራሉ። እነዚህ እጩዎች ከአሁን በፊትም ከጠቅላይ ሚንስትሩ ጋር የተወዳደሩ ናቸው?
ቪዲዮ, የኢትዮጵያ እና የሱዳን መካሰስ እና ፍጥጫ
ለረጅም ጊዜ ወዳጅ ሆነው የቆዩት ጎረቤታሞቹ ኢትዮጵያ እና ሱዳን ግንኙነታቸው ሻክሯል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ደግሞ በይፋ በመውጣት ከመካሰስ አልፈው ወደ ግጭት የሚያመሩ ዛቻዎች እየተሰሙ ነው። ለመሆኑ ሁለቱ ጎረቤታሞችን እዚህ ያደረሳቸው ምንድን ነው?
ቪዲዮ, ከነዳጅ ጋር አብረው ስለሚነሱ ቁልፍ ነገሮች ምን ያህል ያውቃሉ?
ለዓለም የነዳጅ እና ኃይል አቅርቦት መሠረት የሆነው የሆርሙዝ ወሽመጥ መዘጋት የአገራትን ምጣኔ ሃብት ወዳልተጠበቀ ቀውስ እየወሰደው ይገኛል። ከዚህ ጋር በተያያዘ ተደጋግሞ የሚነሳው ድፍድፍ ነዳጅ ምንድን ነው? የብሬንት ነዳጅስ? ዝርዝር መረጃው በዚህ ቪዲዮ እንመለከታለን።
ቪዲዮ, የደብረ ጽዮን በፕሬዝዳንትነት መሰየም ትግራይን ወዴት ይወስዳታል?
በትግራይ ሁለት ፕሬዝዳንቶች ተሹመዋል። ህወሓት የፕሪቶሪያ የግጭት ማቆም ስምምነት መፍረሱን በመጥቀስ ከጦርነት በፊት የነበረውን አስተዳደር መመለሱን አስታውቋል። ሌ/ጄኔራል ታደሰ በሥልጣን ላይ እያሉ ነው ደብረጽዮን ፕሬዝዳንት ሆነው የተሾሙት። ክልሉ እንዴት እዚህ ሁኔታ ላይ ደረሰ? የሌ/ጄነራል ታደሰ ዕጣ ፈንታስ ምን ሊሆን ይችላል?
ቪዲዮ, ቃላት እየተወራወሩ ያሉት ቱርክ እና እስራኤል ወደ ወታደራዊ ግጭት ሊያመሩ ይችላሉ?
ባለፉት ሦስት ዓመታት ቱርክ እና እስራኤል መደበኛ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ከመፍጠር ወደ ቀጥተኛ ወታደራዊ ግጭት እያመራ መሆኑ እየተነገረ ነው። በሁለቱ አገራት መሪዎች መካከል የቃላት ጦርነቱ በቀጠለበት በአሁኑ ወቅት ወታደራዊ ግጭት የመከሰት ዕድል ይኖራል ወይ የሚል ጥያቄን እያስነሳ ነው። የሁለቱ አገራት ውዝግብ ወዴት ያመራ ይሆን?
ቪዲዮ, ለሦስተኛ ጊዜ የመግደል ሙከራ የተደረገባቸው የአሜሪካው ፕሬዝዳንት
ቅዳሜ ምሽት ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና በርካታ የአሜሪካ ባለሥልጣናት በተገኙበት የእራት ግብዣ ላይ ጥቃት ለማድረስ የሞከረ ግለሰብ በፀጥታ ኃይሎች በቁጥጥር ስር ውሏል። ትራምፕን ለመግደል የሚደረግ ሙከራ አዲስ አይደለም። እስካሁን በፕሬዝዳንቱ ላይ የተቃጡት የመግደል ሙከራዎች ምን ይመስላሉ?
አነጋጋሪ ጉዳይ
በሐዋሳ የተከፈተው የመጀመሪያው የእናት ጡት ወተት ባንክ የሚሰጠው አገልግሎት ምንድን ነው?
በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የሆነ የእናት ጡት ወተት ባንክ በሐዋሳ ኮምፕሪሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ውስጥ ተከፈተ። ባንኩ ከለጋሽ እናቶች የተሰበሰበ ወተት የደኅንነት ሂደቶችን አልፎ የሚጠራቀምበት ሲሆን፣ ወተቱ በተለያየ ምክንያት ከእናቶቸቻው የጡት ወተት ማግኘት ለማይችሉ ጨቅላ ሕፃናት ያቀርባል።
የመንግሥት ቅርጽ፣ አንቀጽ 39 እና የአዲስ አበባ ጉዳይ በሀገራዊ ምክክር አጀንዳዎች ውስጥ ተካተቱ
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን በመጪው ሐምሌ ሊካሄድ ቀን በተቆረጠለት አገር አቀፍ ጉባኤ ለውይይት ይፋ የሚሆኑ ስምንት ዋነኛ አጀንዳዎችን ይፋ አደረገ። ኮሚሽኑ ይፋ ካደረጋቸው የምክክር አጀንዳዎች መካከል "የመንግሥት አደረጃጀት ሥርዓት ዓይነት" እና በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 39 የተደነገገው "የራስን ዕድል በራስ የመወሰን መብት" ጉዳዮች ተካትተዋል።
አሜሪካ በትግራይ የሰላም ሂደትን "የሚያደናቅፉ አካላትን" አሳሰበች
በትግራይ የሰላም ሂደትን "እያደናቀፉ ያሉ አካላት" ለውይይት ጥረቶች ትብብር እንዲያደርጉ በአዲስ አበባ የአሜሪካ ኤምባሲ ማሳሰቢያ ሰጠ። በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ፣ የፖለቲካ እና የሲቪል ማኅበረሰብ መሪዎች በፖለቲካ ውይይት ውስጥ መሳተፍ እና የፕሪቶሪያውን ግጭትን በዘላቂነት የማቆም ስምምነት ሙሉ በሙሉ መተግበር እንዳለባቸው አሳስቧል።
የትግራይ ክልል ምክር ቤት የግዳጅ ወታደራዊ አገልግሎትን የያዘው አወዛጋቢ አዋጅ ተግባራዊ እንዲሆን አዘዘ
ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ወደ ሥራ የመለሰው የትግራይ ክልል ምክር ቤት የግዳጅ ወታደራዊ አገልግሎትን እና በሞት የሚያስቀጡ ድንጋጌዎችን የያዘው አዋጅ ተግባራዊ እንዲሆን ትዕዛዝ አስተላለፈ።
በትግራይ የሚካሄደው የግዳጅ ምልመላ፡ ከክልሉ የሚሸሹ እና ለመደበቅ የተገደዱ ወጣቶች
በትግራይ እየተካሄደ ያለው የግዳጅ ወታደራዊ ምልመላ በፈጠረው ስጋት ምክንያት በርካታ ወጣቶች ከክልሉ እየወጡ ወደ ቀሪው የኢትዮጵያ ክፍል እየሸሹ ሲሆን ሌሎች ደግሞ እዚያው ተደብቀው እንደሚገኙ ተናገሩ። አፈሳው ከነዋሪዎች እና ከመብት ድርጅት ውግዘት እየገጠመው ቢሆንም በፈቃደኝነት የሚካሄድ ነው በማለት ህወሓት አስተባብሏል።
ህወሓት ለግዳጅ ወታደራዊ ምልመላ ያወጣውን ረቂቅ ሕግ "በዝባዥ" በማለት ሂውማን ራይትስ ዋች እንዲሰረዝ አሳሰበ
የትግራይ ክልል መሪዎች ለወታደራዊ ግዳጅ ምልመላ ለማድረግ "ኃይል የሚሰጣቸውን" እና ተቃዋሚዎችን እንዲቀጡ "መንገድ የሚጠርግላቸውን" ረቂቅ አዋጅ እንዲሰርዙ ሂውማን ራይትስ ዋች አሳሰበ። የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ሰኔ 16/2018 ዓ. ም. ባወጣው መግለጫ ህወሓት ረቂቅ አዋጁን ያወጣው በፌደራል መንግሥቱ የተሾሙ የክልሉን አስተዳዳሪዎች ከሥልጣን አውርዶ "ከኤርትራ ብሔራዊ የውትድርና አገልግሎት ጋር የሚመሳሰል አፈሳ ከጀመረ በኋላ ነው" ብሏል።
አሜሪካ በህወሓት መሪዎች እና ቤተሰቦቻቸው ላይ የቪዛ ማዕቀብ ጣለች
አሜሪካ በኢትዮጵያ ያለውን ሰላም በማናጋት ውስጥ ተሳታፊ ናቸው ባለቻቸው አክራሪ የህወሓት አባላት እና የቅርብ የቤተሰብ አባሎቻቸው ላይ የቪዛ ክልከላ መጣሏን አስታወቀች። የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ በአክራሪ ህወሓት አባላት እና በኢትዮጵያ መንግሥት መካከል በሰሜን ኢትዮጵያ ግጭት እንዲያገረሽ የሚያደርግ ውጥረት እየተባባሰ መምጣቱን በመግለጽ ይህም "በቀጣናው ያለውን ሰላም እና መረጋጋት የሚያናጋ ነው" ብሏል።
በ10 ዓመት 6 መሪዎች፡ ለምን የዩናይትድ ኪንግደም ጠቅላይ ሚኒስትሮች በቶሎ ይለዋወጣሉ?
ባለፉት ከ300 ዓመታት በላይ በዩናይትድ ኪንግድም 58 ጠቅላይ ሚኒስትሮች ሥልጣን ይዘዋል። ይህም ዕኩል ቢካፈል ለእያንዳንዳቸው ከአምስት ዓመት በላይ የሥልጣን ዘመን ይኖራቸዋል። ነገር ግን ባለፉት 10 ዓመታት ስድስት ጠቅላይ ሚኒስትሮች በሥልጣን ላይ ተፈራርቀዋል። ይህ በአጭር ጊዜ የታየው የበርካታ ጠቅላይ ሚኒስትሮች መለዋወጥ ምክንያቱ ምንድን ነው?
አሸናፊው ብልጽግና እና ተቃዋሚ ፓርቲዎች ስለ ምርጫው ውጤት ምን አሉ?
የሰባተኛው አጠቃላይ ምርጫ አሸናፊ የሆነው ብልጽግና ፓርቲ፤ "ዘላቂ ሰላም እና ፀጥታን ለማስፈን" እንዲሁም "የሕግ የበላይነትን በፅኑ መሠረት ላይ ለመገንባት" በቁርጠኝነት እንደሚሠራ አስታወቀ። አብን ባወጣው መግለጫ አሸናፊው ፓርቲ "በሃይማኖት እና በብሔር ማንነት ላይ ያነጣጠሩ ጥቃቶችን" እንዲያስቆም ሲያሳስብ፤ ኢዜማ ደግሞ ብልጽግና "ፍትሐዊ የፖለቲካ ምኅዳርን ለሁሉም እኩል ተደራሽ" እንዲያደርግ ጠይቋል።
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ፓርቲ በምርጫው ማሸነፍ እና የአዲስ ግጭት ስጋት
ግንቦት 24/2018 ዓ.ም. በተካሄደው አጠቃላይ ምርጫ የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ፓርቲ ብልጽግና አብዛኛውን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት መቀመጫዎችን በማሸነፍ የበላይነትን ይዟል። ይህም ማለት ዐቢይ ለሁለተኛ ዙር የሥልጣን ዘመን በመሪነት መቀጠላቸውን የሚያረገግጥ ነው። የጠቅላይ ሚኒስትሩ በሥልጣን ላይ መዝለቅ በተለይ በምርጫው ባልተሳተፈችው ትግራይ ውስጥ ከህወሓት ጋር ለተፈጠረው ውጥረት ምን ዓይነት መፍትሄ ያስገኝ ይሆን?
የቢቢሲ አማርኛ ዩቲዩብ ቻናልን ይቀላቀሉ
የመካከለኛው ምሥራቅ ጦርነት
የአሜሪካ እና ኢራን ጦርነትን ያስቆማል የተባለው ስምምነት ምን ምን ይዟል?
የአሜሪካ እና ኢራን ከመግባባት ላይ የደረሱበት ሰነድ ይፋ ሆኗል። ስምምነቱ የሆርሙዝ ወሽመጥ እንዲከፈት እንደሚያደርግ እንዲሁም ለወራት የቆየውን ጦርነት ያስቆማል የሚል እምነት አሳድረዋል። ትራምፕ ባለ 14 ነጥቡ ስምምነት "በአፈጻጸም ላይ የተመሠረተ" መሆኑን እና ኢራን ልትጠቀም የምትችለው ስምምነቱን የምታከብር ከሆነ ብቻ ነው ብለዋል። የስምምነቱ ነጥቦች ምን ምን ይዘዋል?
በሆርሙዝ ወሽመጥ ላይ የአሜሪካንን ባሕር ኃይል እየፈተኑ ያሉት የኢራን ትናንሽ ጀልባዎች
ፕሬዝዳንት ትራምፕ የኢራንን ባሕር ኃይል እንዳወደሙ ቢናገሩም፣ ኢራን ትናንሽ ፈጣን ጀልባዎችን በመጠቀም በሆርሙዝ ወሽመጥ የመርከቦችን እንቅስቃሴን መግታት ችላለች። ስለእነዚህ ውጤታማ የኢራን ፈጣን ወታደራዊ ጀልባዎች ምን እናውያለን?
አሜሪካ እና ኢራን ድል እንደተቀዳጁ እያወጁ ባሉበት ጦርነት አሸናፊው ማን ነው?
አሜሪካ ከኢራን ጋር የምታደርገውን ጦርነት ማቆሟን እየተናገረች ነው። በሁለቱ አገራት መካከል የተኩስ አቁም ከተደረገ ከሳምንታት በኋላ ማክሰኞ ዕለት የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ "ኢፒክ ፊውሪ' በማለት የተጠራው ዘመቻ ማብቃቱን ተናግረዋል።በአሜሪካ እና በኢራን መካከል በተደረገው ጦርነት ማን አሸነፈ?
ከየፈርጁ
በድምጻውያን ጉሮሮ ላይ የቆመው ኤአይ የኢትዮጵያን ሙዚቃ መልክ እንዴት ሊለውጠው ይችላል?
በሰው ሰራሽ አስተውሎት (ኤአይ) ተገርበው በአዲስ መልክ የተሠሩ ሙዚቃዎች የዩቲዩብ ገፆችን ወርረዋል። የአንጋፋ እና ተወዳጅ ድምጻውያን የሙዚቃ ሥራዎች አማርኛው በተኮላተፈ የኤአይ አንደበት እየተዘፈኑ ነው። አንዳንዶቹ በመቶ ሺህዎች የሚቆጠሩ ዕይታዎች አሏቸው። የአድማጭን ትኩረት የሳቡም ይመስላሉ። ለመሆኑ የዘመኑ የቴክኖሎጂ ልህቀት በተለይ በሙዚቃው ዘርፍ ምን ያሳጣ፣ ምን ያስገኝ ይሆን? የኢትዮጵያን ሙዚቃስ በምን መልኩ ሊለውጠው ይችላል?
የአሜሪካዋ ግዛት ምክር ቤት ለአድዋ ድል መታሰቢያ ቀን ሰየመ
በአሜሪካ፣ የፔንሲልቪኒያ ግዛት የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ የአውሮፓዊያኑ 'መጋቢት 2' በግዛቱ የአድዋ ድል መታሰቢያ ቀን እንዲሆን የቀረበን የውሳኔ ሐሳብ በከፍተኛ ድምጽ አፀደቀ። ይህ 'ኤችአር 441' የተሰኘው የውሳኔ ሐሳብ የፀደቀው ባለፈው ሳምንት በግዛቲቱ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በተደረገ የድምጽ አሰጣጥ ሥነ ሥርዓት ነው።
ቢቢሲ አማርኛን በዋትስአፕ ላይ ያግኙ
አጃኢብ!
የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ለምን ስለ እናታቸው በአደባባይ አይናገሩም?
የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪን ጆንግ ኡን በምሥጢር ከያዟቸው ነገሮች አንዱ የእናታቸው ጉዳይ ነው። ለ15 ዓመታት በሥልጣን ሲቆዩ አንድም ቀን የእናታቸውን ስም በአደባባይ አንስተው አያውቁም። ይህ ለምን ሆነ?
የተመለሱ ጥያቄዎች
ያለባቸው የጤና ችግር ሕክምና እንዲያጠኑ ያደረጋቸው ኢትዮጵያውያን ወጣቶች
በረከት በቀለ፣ ኪምቢፊዳ በሚል ስም ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ ይታወቃል። ወደ ቲክቶክ ብቅ ከማለቱ አስቀድሞ "በስፓይና ቢፊዳ (spina befida) የተያዝኩ ብቸኛው ሰው እኔ ብቻ እንደሆንኩ ይሰማኝ ነበር" ይላል። የአሊያንስ ፎር በርዝ ዲፌክት መሥራቹ ዶ/ር ነቢያት ተስፋዬም ልክ እንደ በረከት ሁሉ ከስፓይና ቢፊዳ (የነርቭ ዘንግ ክፍተት) ጋር ነው የተወለደው። አሁን 33 ዓመት እንደሆነው የሚናገረው ዶ/ር ነቢያት፣ በተወለደ በ22ኛው ቀን የስፓይና ቢፊዳ የቀዶ ሕክምና ተደርጎለታል። ሁለቱም ወጣቶች ከራሳቸው ህመም ተነስተው ሕክምና ለማጥናት መወሰናቸውን ለቢቢሲ ተናግረዋል።
ኢትዮጵያዊ እና ኬንያዊ አትሌቶች ማራቶንን ከሁለት ሰዓት ባነሰ ጊዜ እንዲጨርሱ ያስቻላቸው ምስጢር ምንድን ነው?
ትናንት እሁድ በለንደን የተካሄደው የማራቶን ውድድር ኬንያዊው ሳባስቲያን ሳዌ እና ኢትዮጵያዊው ዮሚፍ ቀጄልቻ ከሁለት ሰዓት በታች ተከታትለው በመግባት ዓለምን አስደምመዋል።
አስፈላጊ ነገር ግን ጎጂ የሆነውን የጨው አወሳሰዳችንን እንዴት መመጠን እንችላለን?
ጨው ምግባችንን የበለጠ ያጣፍጠዋል። ለሰው ልጅ ሕይወትም አስፈላጊ ነው። በጨው ውስጥ የሚገኘው ሶዲየም በሰውነት ውስጥ የሚኖረውን ትክክለኛውን የውሃ መጠን ለመጠበቅ በጣም አስፈላጊ ነው። ህዋሳትም ንጥረ ምግቦችን እንዲወስዱ ይረዳል። በምግብ ጉዳዮች ላይ የሚያተኩረው የቢቢሲ ወርልድ ሰርቪስ ፕሮግራም “ዘ ፉድ ቼይን” ጨው በሰውነታችን ውስጥ ያለውን ወሳኝ ሚና እና ለአንድ ሰው ከመጠን በላይ የሚባለው የጨው ፍጆታ ምን ያህል ነው የሚለውን ተመልክቷል።
የኢንተርኔት ዳታን በመቆጠብ የቢቢሲ አማርኛ ድረ ገጽን በቀላሉ ማንበብ ይፈልጋሉ?
የቢቢሲ አማርኛን ድረ ገጽ በቀላሉ በመክፈት ዜና እና ታሪኮችን በጽሑፍ ብቻ ያንብቡ!



