[go: up one dir, main page]

ADDIS ABABA REGION-MKC
186 subscribers
137 photos
8 links
ይህ በመሰረተ ክርስቶስ ቤተከርስቲያን የ አዲስ አበባ ክልል ይፋዊ የ ቴሌግራም ገጽ ነው።
Download Telegram
Forwarded from MKC_Official (Ase Yegeta)
#የመሠረተ_ክርስቶስ_ቤተክርስቲያን_አዲስ_የአስተዳደር_መሪዎች_ሾመች

94ኛው የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ጠቅላላ የመሪዎች ጉባኤ ነሐሴ 24 ቀን 2017 ዓ.ም ሲጠናቀቅ ላለፉት ስድስት አመታት ቤተክርስቲያኒቱን ያስተዳድሩ መሪዎችን የምስጋናና እውቅና ሰርተፊኬት በመስጠት በጸሎት ባርኮ ሲሸኝ አዲስ መሪዎችን መርጧል። በሀገር አቀፍ ደረጃ የቤተክርስቲያኒቱን አገልግሎት የሚመራው ይህ ከፍተኛ ስራ አስፈጻሚ ጉባኤ በዕለቱ ሊቀመንበርና ምክትል ሊቀመንበርም ሾሟል።

በዚህም መሠረት ዶ/ር ሰይፈ ወዳጅ በሊቀመንበርነት እንዲሁም ዶ/ር ሳምሶን እስጢፋኖስ በምክትል ሊቀመንበርነት የመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን አስተዳደር መሪዎች ጉባኤን ለቀጣይ ሶስት አመታት የሚመሩ ይሆናል።

ለሁለት ቀናት የቆየው ጠቅላላ ጉባኤ ሲጠናቀቅ መሪዎቹ በጋራ የጌታ እራት ወስደዋል።

"#በወንጌል_ማኅበርተኛ_እሆን_ዘንድ_ስለ_ወንጌል_ሁሉን_አደርጋለሁ" 1ኛ ቆሮ. 9÷23

መረጃዎቻችንን ከዚህ በታች በተቀመጡት አማራጮች ይከታተሉ 👇

በቴሌግራም: https://t.me/MKC_Official
በዩቱብ: https://youtube.com/@mkcmedia2023
በፌስቡክ: https://www.facebook.com/mkcpresidentoffice
3👍1
በመሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን
የአዲስ አበባ ክልል
66ኛው መደበኛ ጠቅላላ የመሪዎች ጉባኤ

በቢሾፍቱ በሚገኘው የመሰረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ሴሚናሪ ተጀመሯል።

ለበለጠ መረጃ
Telegram ላይ ይከታተሉን
5👏2
📍  የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ቤት
       ማስታወቂያ📍

የመሠረተ ክርስቶስ ሴሚናሪ በአዲስ አበባ ክልል መሠረተ ክርስቶስ ጽ/ቤት ባለው ካምፓስ በአማርኛ ቋንቋ የሚሰጠውን የመደበኛ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት እንዲከታተሉና ዲግሪዎን እንዲቀበሉ የተዘጋጀ መርሃ-ግብር !!



📌 የምዝገባ ቀን እና ቦታ:----

መስከረም 10--30 / 2018 ዓ.ም
ዘወትር በስራ ቀንና ሰዓት
ቄራ በሚገኘው የአ/አ መሠረተ ክርስቶስ ቤተክርስቲያን ጽህፈት ቤት


   የመግቢያ መስፈርት:----

📍12ኛ ክፍል ያጠናቀቀ/ች እና የከፍተኛ    ትምህርት መግቢያ ውጤት ያለው/ላት።

📍 ወይም 10+2 የጨረሰ/ች እና ከታወቀ ኮሌጅ ዲፕሎማ ያለው/ላት

📍 አባል/አገልጋይ ከሆነበት/ችበት አጥቢያ ቤተክርስቲያን የህይወት ምስክርነት ማቅረብ የሚችል

📍 እንዲሁም ሁሉንም ማስረጃዎች ዋናውን እና የማይመለስ ፎቶ ኮፒ እና የተማሪው ሁለት ጉርድ ፎቶግራፍ።


   📌 መመዝገቢያ እና የኮርስ ክፍያ:------


መመዝገቢያ:--- ብር 500.00 (አምስት መቶ)
የትምህርት ክፍያ:---- በኮርስ ብር 750.00 (ሰባት መቶ ሃምሳ)
ዛሬ ኅዳር 6 ቀን 2018 ዓ.ም በክልላችን ሥር ካሉ አጥቢያዎች ለመጡ 50 ለሚደርሱ ሠልጣኞች "ዲጂታል ሚሽን" በሚል ርዕስ በክልሉ የወንጌል ሥርጭትና ቤተክርስቲያን ተከላ አዘጋጅነት የአሰልጣኞች ሥልጠና በንፋስ ስልክ መሠረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን አዳራሽ ተሰጥቶአል።