Forwarded from MKC_Official (Asalefew Wolde)
#የምዕራብ_አዲስአበባ_አጥቢያ_ባለ_8_ወለል_ህንጻ_ለመገንባት_የመሰረት_ድንጋይ_አስቀመጠች
በመሠረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን የምዕራብ አዲስ አበባ አጥቢያ ባላት ይዞታ ላይ ባለ 8 ወለል ህንጻ ለመገንባት ነው በዛሬው እለት የመሰረት ድንጋይ ያኖረችው።
አጥቢያዋ የመሰረት ድንጋዩን ያኖረችው የመሠረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ፕሬዚዳንት መጋቢ ደሳለኝ አበበና የመሠረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ሊቀመንበር ዶ/ር ሰይፈ ወዳጅ በተገኙበት ነው። በተጨማሪም በስነ ስርዓቱ ላይ የአዲስአበባ ክልል ዋና ጸሐፊ መጋቢ ግርማ ጊቢሶ እና የአጥቢያዋ መሪዎችና አገልጋዮች ተገኝተዋል።
የምዕራብ አዲስአበባ አጥቢያ በ1978 ዓ.ም የተተከለችና በከተማዋ ካሉ አንጋፋ አጥቢያዎች መካከል አንዷ ስትሆን በዛሬው ዕለት የመሰረት ድንጋዩ የተጣለውን ህንጻ ገንብቶ ለማጠናቀቅም ከ180 ሚልዮን ብር በላይ ወጪ እንደሚሆን ይጠበቃል።
መረጃዎቻችንን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ይከታተሉ 👇
በቴሌግራም: https://t.me/MKC_Official
በዩቱብ: https://youtube.com/@mkcmedia2023
በፌስቡክ: https://www.facebook.com/mkcpresidentoffice