[go: up one dir, main page]

ADDIS ABABA REGION-MKC
186 subscribers
137 photos
8 links
ይህ በመሰረተ ክርስቶስ ቤተከርስቲያን የ አዲስ አበባ ክልል ይፋዊ የ ቴሌግራም ገጽ ነው።
Download Telegram
🔖 እንኳን ደስ አለን ....................... እንኳን ደስ አላችሁ

ሰላም የተወደዳችሁ።

📢 ዛሬ ህዳር 08/2018 ዓ.ም የአዲስ አበባ ክልል መሠረተ ክርስቶስ ቤ/ክ የመጽሐፍ ቅዱስ ት/ቤታችን መደበኛ አገልግሎት መጀመሩን በደስታ እናበስራለን‼️

ይህንን ታላቅ ቸርነት ላደረገልን አምላካችን እግዚአብሔር ብዙ ክብርና ምስጋና ይሁን 🙏🙏🙏

ወገኖች እንኳን ደስ ያላችሁ.... እንኳን ደስ አለን እያልን የዘውትር ማበረታቻችሁና ጸሎታችሁ እንዳይለየን አደራ እላለሁ🙏
ብዙ በረከት!!

AARMKC
👍31👏1
Forwarded from Girma Gibisso
Forwarded from Mikiyas Bezabh
ክብር ለእግዚአብሔር ይሁን‼️

ታህሳስ 05/2018 ዓ.ም በመሠረተ ክርስቶስ ሴሚናሪ የአዲስ አበባ ክልል መጽሐፍ ቅዱስ ት/ቤት ይፋዊ የመክፈቻ እና የገቢ ማሰባሰቢያ ተካሔደ። 

የአጥቢያ መሪዎች እና የአገልግሎት ተጠሪዎች; እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው የክብር እንግዶች በተገኙበት የመክፈቻ ፕሮግራም የተካሄደ ሲሆን; አጥቢያዎች እና እንግዶች በመጽሐፍ ቅዱስ ት/ቤቱ መከፈት የተሰማቸውን ደስታ እና አብሮነታቸውን በመግለጽ የፍቅር ስጦታቸውን አበርክተዋል።

ተወዳጆች ሆይ በእግዚአብሔር መንግስት ሥራ ውስጥ አጋርነታችሁን በደስታ ስላሳያችሁን እናመሰግናለን  ክብረት ይስጥልን 🙏🙏
6👍2
Forwarded from MKC_Official (Asalefew Wolde)
#የምዕራብ_አዲስአበባ_አጥቢያ_ባለ_8_ወለል_ህንጻ_ለመገንባት_የመሰረት_ድንጋይ_አስቀመጠች

በመሠረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን የምዕራብ አዲስ አበባ አጥቢያ ባላት ይዞታ ላይ ባለ 8 ወለል ህንጻ ለመገንባት ነው በዛሬው እለት የመሰረት ድንጋይ ያኖረችው።

አጥቢያዋ የመሰረት ድንጋዩን ያኖረችው የመሠረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ፕሬዚዳንት መጋቢ ደሳለኝ አበበና የመሠረተ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ሊቀመንበር ዶ/ር ሰይፈ ወዳጅ በተገኙበት ነው። በተጨማሪም በስነ ስርዓቱ ላይ የአዲስአበባ ክልል ዋና ጸሐፊ መጋቢ ግርማ ጊቢሶ እና የአጥቢያዋ መሪዎችና አገልጋዮች ተገኝተዋል።

የምዕራብ አዲስአበባ አጥቢያ በ1978 ዓ.ም የተተከለችና በከተማዋ ካሉ አንጋፋ አጥቢያዎች መካከል አንዷ ስትሆን በዛሬው ዕለት የመሰረት ድንጋዩ የተጣለውን ህንጻ ገንብቶ ለማጠናቀቅም ከ180 ሚልዮን ብር በላይ ወጪ እንደሚሆን ይጠበቃል።

መረጃዎቻችንን በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያ አማራጮች ይከታተሉ 👇

በቴሌግራም: https://t.me/MKC_Official
በዩቱብ: https://youtube.com/@mkcmedia2023
በፌስቡክ: https://www.facebook.com/mkcpresidentoffice